Posts

Showing posts from 2013

የሥላሴዎች እርግማን፤ (አንድ) አዳክሞ ማደህየት መስፍን ወልደ ማርያም

አዳክሞ ማደህየት የወያኔ ትልቅና ዋና መሣሪያ ሆኖ አገልግሎአል፤ ወያኔ ከኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አርባ ያህል መምህራንን ያስወጣው ገና በጠዋቱ ነበር፤ ከቴሌ ከመብራት ኃይልና ከባንክ ሰዎችን እየመነጠረ ያስወጣው በዘር አመካኝቶ ቢሆንም በትምህርታቸውና በልምዳቸው የጠጠሩበትን ሰዎች እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ እንደፐሮፌሰር ዓሥራት ያለውን በሁለት የታወቁ የእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች የተመሰከረለትን ሰው በችሎታ ማነስ ብሎ ማስወጣት ችሎታ ያነሰው ማን አንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል፤ እነዚህን የተለያዩ ባለሙያዎች በማስወጣት ወያኔ ሰዎቹን አልጎዳም፤ ሁሉም የተሻለ ኑሮና የተሻለ የሥራ እርካታ አግኝተዋል፤ የተጎዱት መሥሪያ ቤቶቹ ናቸው፤ ከወያኔ ጋር ወደኋላ የሄደችው ኢትዮጵያ ነች፤ ወደኋላ የሄደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በመሬት ያየነው እንደሆነ የወልቃይት-ጸገዴና የራያ-ቆቦ ድንበር ለትግራይ በሚጠቅም መልኩ ቢለወጥና ጎንደርንና ወሎን ቢያስቀይምም አዲስ የመሬት ድልድልን ፈጥሮአል፤ ከመሬቱም ጋር የ‹‹አማራ›› ሕዝብ ቁጥር እንዲቀንስ ሆኖአል፤ ይህ ሁሉ ማዳከም አይሆንም? አዳክሞ ማደህየት አይሆንም? ምርጥ የአገሪቱ መሬት ለውጭ አገር ባለሀብቶች በቸርነት የሚቸበቸበው ገበሬውን ለማዳከምና ወደኩሊነት ለመለወጥ አይደለም? ወደኩሊነት በመለወጥ የራሱን ዕድል በራሱ በመወሰን ፋንታ ሌላ ሰው፣ ምናልባትም ባዕድ ይወስንለታል፤ ከዚህ የበለጠ አዳክሞ ማደህየት ምን አለ? አንድን ሕዝብ ካዳከሙ በኋላ ማደህየቱ በጣም ቀላል ነው፤ ደርግ ባያውቅበትም በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ሰይፍ ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሞክሮ ነበር፤ የደርግ ችግር ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሀብታሞቹን በጠመንጃ ማደህየት ግዴታ አድርጎ መከተሉ ነበር፤ መሬት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ነው ብሎ አላቆመም፤ ወይም በባለቤቱ...

የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት መስፍን ወልደ ማርያም

የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን በአሸነፈች ጊዜ ደግሞ በቴክሳስ የሚኖር ከአንድ ግሪክ ገንፍሎ የወጣው ንግግር በጣም ልብን የሚነካ ነበር፤ ለዚህ አርመንና ለዚህ ግሪክ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዘር የተላለፈላቸው አይመስለኝም፤ ስለዚህም አሜሪካ የሚወለዱትም ኢትዮጵያውያን ልጆች እናቶቻቸው ሳያውቁ ከውስጣቸው የሚያስተላልፉላቸው ስሜት ኢትዮጵያዊነታቸውን ይገነባው ይሆናል፤ እንደሚመስለኝ የሚሞቱለት መሬት ከውስጥ ከነፍስ ጋር በተገናኘ ስሜት የተቆራኘ ነው፤ መሬቱንና ስሜቱን ምን አገናኛቸው? ምን አቆራኛቸው? እንዴት ተቆራኙ? የሚሉትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር እዚህ ቦታው አይደለም፤ ለዚች መሬት የሞቱላት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸውን አምነን በመቀበል እንነሣ፤ ምናልባትም አብዛኛዎቹ ቁራጭ መሬትም አልነበራቸውም፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ለመቃብር ያህል ሁለት ክንድ መሬት አንኳን አላገኙም፤ በተሰለፉበት ወድ...

የአማራ ሕዝብ ቁጥር የኮሚሽኑ መዘባበቻ መሆኑ ቀጥሏል፡፡

• ኮሚሽኑ የአማራ ክልል ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ •ኮሚሽኑ ስህተቱን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም ብሏል በ2001 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው ሦስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከተገመተው በሁለት ሚሊዮን አንሶ በመገኘቱ የፈጠረውን ውዝግብና ዓይን ያወጣ ዘር ማጥፋ በዝምታ የሚታለፍ የመሰለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሉ ሕዝብ ብዛት ላይ የማስመሰ ያ ድጋሚ ጥናት እንዲካሄድ በወቅቱ በወሰነው መሠረት ጥናት ተካሂዶ፣ የክልሉ ሕዝብ ቁጥር በ2.1 ሚሊዮን ከፍ ብሎ እንዲስተካከል የሚያስችል የዕድገት ምጣኔ ተገኘ የሚል ቀልድ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን በፓርላማው ውሳኔ መሠረት በሁለት ቆጠራዎች መካከል የሚደረግ ‹‹ኢንተር ሴንሳል›› ጥናት በ2004 ዓ.ም. በማካሄድ ያገኘውን ውጤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ና ታዋቂው አገር ሻጭ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በ1999 ዓ.ም. እና በቀጣዩ ቆጠራ አጋማሽ ላይ በተደረገው ጥልቅ ጥናት በተገኘው ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ከሌሎች ክልሎችና ከአገር አቀፍ ምጣኔው በታች 1.73 በመቶ መሆኑ ስህተት ነበር ብለዋል፡፡ ትክክለኛው የክልሉ የዕድገት ምጣኔም ከአገር አቀፍ ምጣኔው ጋር ተቀራራቢ የ2.3 በመቶ ዕድገት እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡ በዚህ መሠረት በተስተካከለው የ2.3 ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ሲሰላም የአማራ ክልል ሕዝብ በ2004 ዓ.ም. 19.2 ሚሊዮን መሆኑን...