የአማራ ሕዝብ ቁጥር የኮሚሽኑ መዘባበቻ መሆኑ ቀጥሏል፡፡
• ኮሚሽኑ የአማራ ክልል ሕዝብን ይቅርታ ይጠይቅ ተባለ •ኮሚሽኑ ስህተቱን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም ብሏል በ2001 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው ሦስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከተገመተው በሁለት ሚሊዮን አንሶ በመገኘቱ የፈጠረውን ውዝግብና ዓይን ያወጣ ዘር ማጥፋ በዝምታ የሚታለፍ የመሰለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሉ ሕዝብ ብዛት ላይ የማስመሰ ያ ድጋሚ ጥናት እንዲካሄድ በወቅቱ በወሰነው መሠረት ጥናት ተካሂዶ፣ የክልሉ ሕዝብ ቁጥር በ2.1 ሚሊዮን ከፍ ብሎ እንዲስተካከል የሚያስችል የዕድገት ምጣኔ ተገኘ የሚል ቀልድ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን በፓርላማው ውሳኔ መሠረት በሁለት ቆጠራዎች መካከል የሚደረግ ‹‹ኢንተር ሴንሳል›› ጥናት በ2004 ዓ.ም. በማካሄድ ያገኘውን ውጤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ አቅርቧል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ና ታዋቂው አገር ሻጭ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በ1999 ዓ.ም. እና በቀጣዩ ቆጠራ አጋማሽ ላይ በተደረገው ጥልቅ ጥናት በተገኘው ውጤት መሠረት የአማራ ክልል ሕዝብ ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ከሌሎች ክልሎችና ከአገር አቀፍ ምጣኔው በታች 1.73 በመቶ መሆኑ ስህተት ነበር ብለዋል፡፡ ትክክለኛው የክልሉ የዕድገት ምጣኔም ከአገር አቀፍ ምጣኔው ጋር ተቀራራቢ የ2.3 በመቶ ዕድገት እንዳለው በጥናቱ መረጋገጡን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡ በዚህ መሠረት በተስተካከለው የ2.3 ዓመታዊ የዕድገት ምጣኔ ሲሰላም የአማራ ክልል ሕዝብ በ2004 ዓ.ም. 19.2 ሚሊዮን መሆኑን...