Posts

Showing posts from August, 2013

የሥላሴዎች እርግማን፤ (አንድ) አዳክሞ ማደህየት መስፍን ወልደ ማርያም

አዳክሞ ማደህየት የወያኔ ትልቅና ዋና መሣሪያ ሆኖ አገልግሎአል፤ ወያኔ ከኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አርባ ያህል መምህራንን ያስወጣው ገና በጠዋቱ ነበር፤ ከቴሌ ከመብራት ኃይልና ከባንክ ሰዎችን እየመነጠረ ያስወጣው በዘር አመካኝቶ ቢሆንም በትምህርታቸውና በልምዳቸው የጠጠሩበትን ሰዎች እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው፤ እንደፐሮፌሰር ዓሥራት ያለውን በሁለት የታወቁ የእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች የተመሰከረለትን ሰው በችሎታ ማነስ ብሎ ማስወጣት ችሎታ ያነሰው ማን አንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል፤ እነዚህን የተለያዩ ባለሙያዎች በማስወጣት ወያኔ ሰዎቹን አልጎዳም፤ ሁሉም የተሻለ ኑሮና የተሻለ የሥራ እርካታ አግኝተዋል፤ የተጎዱት መሥሪያ ቤቶቹ ናቸው፤ ከወያኔ ጋር ወደኋላ የሄደችው ኢትዮጵያ ነች፤ ወደኋላ የሄደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በመሬት ያየነው እንደሆነ የወልቃይት-ጸገዴና የራያ-ቆቦ ድንበር ለትግራይ በሚጠቅም መልኩ ቢለወጥና ጎንደርንና ወሎን ቢያስቀይምም አዲስ የመሬት ድልድልን ፈጥሮአል፤ ከመሬቱም ጋር የ‹‹አማራ›› ሕዝብ ቁጥር እንዲቀንስ ሆኖአል፤ ይህ ሁሉ ማዳከም አይሆንም? አዳክሞ ማደህየት አይሆንም? ምርጥ የአገሪቱ መሬት ለውጭ አገር ባለሀብቶች በቸርነት የሚቸበቸበው ገበሬውን ለማዳከምና ወደኩሊነት ለመለወጥ አይደለም? ወደኩሊነት በመለወጥ የራሱን ዕድል በራሱ በመወሰን ፋንታ ሌላ ሰው፣ ምናልባትም ባዕድ ይወስንለታል፤ ከዚህ የበለጠ አዳክሞ ማደህየት ምን አለ? አንድን ሕዝብ ካዳከሙ በኋላ ማደህየቱ በጣም ቀላል ነው፤ ደርግ ባያውቅበትም በማርክሳዊ-ሌኒናዊ ሰይፍ ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሞክሮ ነበር፤ የደርግ ችግር ደሀዎችን ከደሀነት ለማውጣት ሀብታሞቹን በጠመንጃ ማደህየት ግዴታ አድርጎ መከተሉ ነበር፤ መሬት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ነው ብሎ አላቆመም፤ ወይም በባለቤቱ...