Posts

Showing posts from 2014

የአፍሪካ ነገር – የኢትዮጵያ ነገር መስፍን ወልደ ማርያም

በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው። በአለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የታየው የሥልጣን ሽኩቻ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች የእድገት ማነቆ ሆኖ ቆየ፤ ከአውሮፓውያን ቄሣራዊ ኃይሎች ቅኝ አገዛዝ ነጻ ሲወጡ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው አገሮች ዛሬ ቆመው ቀርተዋል፤ በሰሜን አፍሪካ አልጂርያና ቱኒስያ እንደፈረንሳይ የሚቆጠሩ ናቸው ይባል ነበር፤ እነዚህ ትልልቅ አገሮች ለሁለት ለሁለት ሰዎች የማይበቁ ሆነው የመከራ አገሮች ሆነዋል፤ ከፈረንሳይ ጋር በአደረጉት መራራ ትግል ሕዝቦቹ የከፈሉትን መስዋእትነትና ትግላቸው አሳድሮባቸው የነበረውን የላቀ ተስፋ መሪዎቹ ዋጋ አልሰጡትም፤ (ተመስገን ደሳለኝ በፋክት ቁጥር 33 ‹‹የሕወሓት ሰማዕታት አጭር ማስታወሻ፣) በዚህም ምክንያት እነሱ ለአንድ ወንበር ሲፎካከሩና ተወዳዳሪዎቻቸውን አስረውም ሆነ ገድለው ወንበሩን ለብቻቸው ሲይዙት ቆይተዋል። በአንድ በኩል ከወንበሩ በሚመነጨው ኃይልና ሀብት መከታን የሚያገኙ መስሏቸው በነበራቸው ተስፋ፣ በሌላ በኩል በምዕራባውያን ኃይሎች ላይ ተማምነው ሕዝባቸውን በመናቃቸው በአረብ አገሮች መሪዎች ላይ በቅርቡ በተከሰተው ወረርሺኝ ብዙዎች ከወንበራቸው ተደፍተዋል፤ የሁ...

በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18 By Prof. Mesfin Woldemariam

ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው፡፡ የማላውቃቸው ነገሮች ዝርፊያ በየፈርጁ! በቃሊቲ ወህኒ ቤት የትምህርት ቤት የነበረ ሕንጻ ወደእስር ቤት መለወጡን አይቼ ነበር፤ አሁን ደግሞ የሕዝብ ትምህርት ቤት ለግለሰብ መሸጡን አወቅሁ፤ ጡንቻ ነው እንጂ ትምህርት ምን ዋጋ አለው! ይህ ሁሉ ዝርፊያ፣ ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም ሌላው ሁሉ ጮሆ አቤት ለማለት እንኳን የማይደፍር ሆኖ ነው ወይስ የሕግ አስከባሪ በአገሩ ጠፍቶ ነው? ድፍረቱን አጥፍተውት ከሆነ በከበደ ሚካኤል ብእር ፋሺስቱ የተናገረው ልክ ነበር ማለት ነው፤– መሬት የሁሉ ነች ባለቤት የላትም! ኃይለኛ እየሄደ ያስገብራል የትም፤ መሬት ባለቤት ከሌላት ሰዎች አገር የላቸውም ማለት ነው፤ አገር የሌላቸው ሰዎች ዶላር ይዞ ለመጣ ቤታቸውንና መሬታቸውን እንዲያስረክቡ ይገደዳሉ፤ ሕገ መንግሥቱ መሬት የሕዝብና የመንግሥት ነው ስለሚል ባለዶላር ወይም ባለሀብት ሕዝብ የሚለውን ይተካል። ኑዛዜ ኤርምያስን ያነበበ የወያኔ ባለሥልጣኖችን ራቁታቸውን ያያቸዋል፤ ካልዋሸ ራሱንም ራቁቱን ቆሞ ያየዋል፤ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ደጋግሜ እንዳልሁት ጨቋኝና ተጨቋኝ ተደጋጋፊዎች ናቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ በኑዛዜ ኤርምያስ ላይ ጎልቶ ለሚታየው የጨቋኞቹ ቆራጥነትና ጭካኔ ጉልበቱን ከየት አገኙት ቢባል መልሱ ቀላል ነው፤ ከተጨቋኞቹ ተንጋልሎ ጭቆናን ከመቀበል ችሎታ ነው፤ድፍረታቸውን አደንቃለሁ፤ድፍረታቸው ወደወንበሩ ስቧቸው ወጡበትና (ተቀመጡበት እንዳልል አልተመቻቸውም፤) ዘመኑ የፍርሃት፣ እንቅልፍ አ...

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ By Prof. Mesfin W/Mariam

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው። የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመ...

አይ አበሻ! አበሻና ቀጥታ መስመር By Prof. Mesfin W/Mariam

አበሻና ቀጥታ መስመር አይተዋወቁም፤ ቀጥታ መስመር መጀመሪያ አለው፣ መጨረሻም አለው፤ አበሻ እንዲህ ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አይወድም፤ እልቅ ሲል ጭር ይልበታል፤ አበሻ የባህርዩ የሆነውና የሚስማማው ክብ መስመር ነው፣ ክብ መስመር መጀመሪያ የለው፣ ማለቂያ የለው፣ ሲዞሩ መዋል ነው፤ አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፤ ቤቱ ክብ ነው፣ እንጀራው ክብ ነው፣ ዳቦው ክብ ነው፣ ድስቱ ክብ ነው፣ ጋኑም ክብ ነው፤ ክብ ያልሆነ ነገር አበሻ ምን አለው? አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፣ አዙሪት ነው፣ ታሪኩም አዙሪት ነው፣ ሄደ የተባለው ሁሉ ተመልሶ ይመጣል። አበሻ ማለት አዙሪት ነው፣ አዙሪት ማለትም አበሻ ነው። የእንግሊዝ ወይም የሩስያ ወታደሮችን ሰልፍ ስታዩ ቀጥታ መስመር ምን እንደሆነ ተገነዘባላችሁ። የአበሻ ወታደሮችስ? ተለያይቶ የተገጣጠመ ክብ መስመር? አበሻ በመስመር መሄድም ሆነ መቆም አይሆንለትም። አበሻ ቀጥታ መሰመር ሲያጋጥመው የሚታየው ተለምጦ ነው፣ ክብ ሆኖ ነው፣ መጀመሪያ የሌለው፤ መጨረሻም የሌለው በፈለገበት በኩል ሊገባበትና በፈለገበት በኩል ሊወጣበት የሚያስችለው ክብ ሲሆን ነው፤ ሰዎች ተራ ይዘው በመስመር እንዲጠብቁ በሚደረግበት ግዜ አበሻ ጭንቀቱ ነው፤ እንዴት ብሎ ጀርባውን ለማያውቀው ሰጥቶ ከፊቱ ደግሞ አንድ የማያውቀው ሰው ተደንቅሮ በሰላም መቆም ይችላል? አንዱ ደፋር ከኋላው መጥቶ ቀድሞት ቢሄድ ግድ የለውም፤ ለነገሩ ራሱም ቢሆን ፈርቶ ነው እንጂ ያደርገው ነበር! የድሮዎቹን ሰዎች ጭንቀታቸውን ለመቀነስ አንተ ቅደም አንተ ቅደም እየተባባሉ የተራውን ቀጥታ መስመር ይቆለምሙት ነበር፤ የዛሬው የሰለጠነው ትውልድ አንተ ቅደም ብሎ ነገር አያውቅም፣ ሁሉም በየፊናው ለመቅደም ሲሞክር መተራመስ ነው፤ መተራመስ ቀጥታ መስመርን ድራሹን ማጥፋት ነው። አበሻ ለቀጥታ...

Free Zone9 Bloggers

Image
በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ የዞን 9 ወዳጆች አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው! ራሳችሁን ፎቶ አንስታችሁ በመለጠፍ አጋርነቱን ተቀላቀሉ! Zone9 friends showing solidarity from all over the world.join them post your pictures and show that you care. Blogging is not a crime! #Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem

"Ye Addis Ababa Anbeta" by Fike Man

"የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ተከትሎ የአንበጣ መንጋ አዲስ አበባን ወሯታል። መንጋዉ የተከሰተዉ የነዉጥ ሃይሎች የሰዉ መንጋ ማሰለፍ ሲያቅታቸዉ ንፁሃን አንበጦችን የሴራቸዉ ተባባሪ በማድረግ ነዉ። በቁጥጥር ስር የዋሉ አንዳንድ አንበጦች እንደገለፁት አዲስ አበባን ልንወር የቻልነዉ ፊንፊኔ ዙሪያ ያለዉ መዋያ መስካችን በአዲሱ ማስተር ፕላን በመካተቱ ከቀያችዉ ሳትፈናቀሉ ቅድሚያ መከላከል ዉሰዱ በማለት በተደረገ የዉጪ ሃይሎች ቅስቀሳ እንደሆነ ተናግረዋል። በልማቱ ተጠቃሚ የሆኑ አንበጣ እገሌ አባ በለዉ ስለተከሰተዉ መንጋ ነዉጥ ናፋቂዎች ያስነሱት መሆናቸዉን የገለፁ ሲሆን አክለዉም እኛ አንበጣዎች ከኪሏችን በላይ ልንበላ የቻልነዉ ልማቱ በፈጠረልን ምቹ ሁኔታ ነዉ ብለዋል። " የዛሬ 2:00 ሰአት ዜና