Posts

Showing posts from July, 2014

የወያኔ ጥላቻ ፍሬ By Prof. Mesfin W/Mariam

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው። የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመ...

አይ አበሻ! አበሻና ቀጥታ መስመር By Prof. Mesfin W/Mariam

አበሻና ቀጥታ መስመር አይተዋወቁም፤ ቀጥታ መስመር መጀመሪያ አለው፣ መጨረሻም አለው፤ አበሻ እንዲህ ተጀምሮ የሚያልቅ ነገር አይወድም፤ እልቅ ሲል ጭር ይልበታል፤ አበሻ የባህርዩ የሆነውና የሚስማማው ክብ መስመር ነው፣ ክብ መስመር መጀመሪያ የለው፣ ማለቂያ የለው፣ ሲዞሩ መዋል ነው፤ አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፤ ቤቱ ክብ ነው፣ እንጀራው ክብ ነው፣ ዳቦው ክብ ነው፣ ድስቱ ክብ ነው፣ ጋኑም ክብ ነው፤ ክብ ያልሆነ ነገር አበሻ ምን አለው? አበሻ ነገሩ ሁሉ ክብ ነው፣ አዙሪት ነው፣ ታሪኩም አዙሪት ነው፣ ሄደ የተባለው ሁሉ ተመልሶ ይመጣል። አበሻ ማለት አዙሪት ነው፣ አዙሪት ማለትም አበሻ ነው። የእንግሊዝ ወይም የሩስያ ወታደሮችን ሰልፍ ስታዩ ቀጥታ መስመር ምን እንደሆነ ተገነዘባላችሁ። የአበሻ ወታደሮችስ? ተለያይቶ የተገጣጠመ ክብ መስመር? አበሻ በመስመር መሄድም ሆነ መቆም አይሆንለትም። አበሻ ቀጥታ መሰመር ሲያጋጥመው የሚታየው ተለምጦ ነው፣ ክብ ሆኖ ነው፣ መጀመሪያ የሌለው፤ መጨረሻም የሌለው በፈለገበት በኩል ሊገባበትና በፈለገበት በኩል ሊወጣበት የሚያስችለው ክብ ሲሆን ነው፤ ሰዎች ተራ ይዘው በመስመር እንዲጠብቁ በሚደረግበት ግዜ አበሻ ጭንቀቱ ነው፤ እንዴት ብሎ ጀርባውን ለማያውቀው ሰጥቶ ከፊቱ ደግሞ አንድ የማያውቀው ሰው ተደንቅሮ በሰላም መቆም ይችላል? አንዱ ደፋር ከኋላው መጥቶ ቀድሞት ቢሄድ ግድ የለውም፤ ለነገሩ ራሱም ቢሆን ፈርቶ ነው እንጂ ያደርገው ነበር! የድሮዎቹን ሰዎች ጭንቀታቸውን ለመቀነስ አንተ ቅደም አንተ ቅደም እየተባባሉ የተራውን ቀጥታ መስመር ይቆለምሙት ነበር፤ የዛሬው የሰለጠነው ትውልድ አንተ ቅደም ብሎ ነገር አያውቅም፣ ሁሉም በየፊናው ለመቅደም ሲሞክር መተራመስ ነው፤ መተራመስ ቀጥታ መስመርን ድራሹን ማጥፋት ነው። አበሻ ለቀጥታ...