Posts
Showing posts from 2017
ሐተታ አድዋ በ በእውቀቱ ስዩም
- Get link
- X
- Other Apps
የአድዋ ድልን ከድንበር ሉአላዊነት ጋር አያይዞ መተንተን የተለመደ ነው፡፡ ድሉ አነሠ በዛ የሚለው ጭቅጭቅ ከዚህ መሠረት ይፈልቃል፡፡ በኔ ግምት የአድዋ ድል ትልቅ ጭብጥ ‹‹የሰውነት ክብር›› ይሰኛል፡፡ ቀደምቶቻችን ወደ አድዋ የጋለቡት በግፍ የተነጠቁትን የሰውነት መታወቂያ ለማስመለስ ነው፡፡ እንዲያውም ሰው መሆናቸውን በማያዳግም መንገድ ያረጋገጡት አድዋ ላይ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወገኖቼ!! ሰው መሆንን ማረጋገጥ ቀላል ነገር አይምሰላችሁ፡፡ አባቶቻችን ከአውሮፓውያን ጋር የሚጋሩትን ግን ደግሞ ከአውሮፓውያን ቀድመው የሚያውቁትን ቅዱስ መጽሐፍ ጠቅሰው ሁላችንም ያዳም ልጆች ነነ ይሉ ነበር፡፡ እና ያዳም ልጆች ነነ ብለው የሚያምኑ ፈረንጆች ቢቸገሩ የሚደርሱላቸው፣ ቢጠቁ የሚታደጓቸው ወንድሞቻቸው እንደሆኑ ያስቡ ነበር፡፡ በርግጥም የሃይማኖት አንድነት የቀለም ልዩነትን ደምስሶ አዳማዊ ወንድማማችነትን ያስገኘበት የዘመን ምዕራፍ ነበር፡፡ ክርስቶፈር ደጋማ የተባለ የፖርቹጋል ነፍጠኛ ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈሰሰው የማተብ አንድነት ስለገፋፋው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ባንድ ወቅት የሚያገለግል የኑሮ ዋስትና በሌላው ዘመን አያገለግልም፡፡ ሁላችንም ያዳም ልጆ ነነ የሚለው የዝምድና ውል ከእለታት አንድ ቀን ያገልግሎት ዘመኑ አለቀ፡፡ በ1548 ተወልዶ በ1600 እንደጧፍ የተቃጠለው ዦርዳኖ ቡርኖ የተባለ የጣልያን መናፍቅ ‹‹ኢትዮጵያውያን ያዳም ልጆች አይደሉም፤ ቅድመ-አዳማዊያን ናቸው እንጂ›› ብሎ ፃፈ፡፡ በቡርኖ ዘመን ኢትዮጵያ የጥቁር ዘር ሁሉ የወል ስሙ ነው፡፡ ቅድመ አዳማዊ ማለት ደሞ በአዳምነት ማዕረግ ያልደረሠ ጅምር ፍጡር ማለት ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ጥቁሮች በእግዜር አምሳል የተፈጠሩ አይደሉም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሳል፡፡ ያለማለዘቢያ ለመግለፅ፣ ጥቁሮች ከእንሥሣትና...
መግለጫ በኢትዮጵያ፡ ትናንት እና ዛሬ By Zelalem Kibret
- Get link
- X
- Other Apps
የጋዜጣዊ መግለጫ እና የአቋም መግለጫ ነገር ሁሌ እንዳስገረመኝ ነው፡፡ እንዴት ብሎ መጠየቅ መልካም ነው አበው እንደሚሉት “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ነውና ነገሩ፡፡ ደስታ ተክለወልድ “ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት” በተሰኝው መፅሃፋቸው መግለጫ የሚለውን ቃል “ማስታወቂያ መንገሪያ ነገር ወይም የመጽሐፍ መግለጫ ለጠንቋይ የሚሰጥ ገንዘብ ነው” ብለው ይፈቱታል፡፡ ይህ ትርጉም በዕውነት መግለጫ አሁን ካለው ትርጉም በ እጅጉ ይርቃል ዛሬ መግለጫ ሌላ ናት እንደ ሃሳብን ማስታወቂያ እንደ ሆኔታን መገምገሚያ ፡፡ “መግለጫዎችን” ስሰማ ግራሞቴን የሚጭሩት የቃላቶቹ አመራረጥ፣ የሃሳቦቹ አስቂኝነት፣ የባለ መግለጫዎቹ ማንነት ወዘተ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ደርግ እንዲህ ብሎ መግለጫ ይሰጥ ነበር” <<በጩኸት የፈረሰች ከተማ እያሪኮ ብቻ ነች !!!>> <<ነጭ ኑግ ጥቁር ወተት አቅርቡልኝ ለሚል ህዝብ አቢዮታዊ እርምጃ እንጅ በ Demand-Supply ጨዋታ ጊዜያችንን አናጠፋም !!!>> <<የመርጦ ለማሪያም ከተማ ህዝብ የሬጋንን አስተዳደር አወገዘ የአለም ሰራተኞችም እንዲተባበሩ ጋበዘ!!! >> … እነ ጋሽ መለስ ወደ ስልጣን መጡና ደግሞ ህዝቡን “ልማት ወይም ሞት” ምናምን ብለው አስጨፈሩት መግለጫቸውንም እንዲህ አስከተሉ: ዘንድሮ በተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ላይ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ ♥ እኛ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ምንም እንኳን ♥ፍቅራችን♥ የ 20 ዓመት (ከ1983 ዓ.ም) ለጋ ፍቅር ቢሆንም፣ ♥በፍቅራችን♥ መሃል የሚገቡት...
የበጋው መብረቅ ይናገራል By Zelalem Kibret
- Get link
- X
- Other Apps
በ15 ዓመት ዕድሜው ጠላትን እፋለማለሁ ብሎ የተነሳ፣ ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ ጠላት ሊይዝ ሲያሳድደው ሲያሻው ጭልሞ ጫካ ውስጥ ዛፍ ላይ መሰላል ሰርቶ እየተደበቀ፣ ሲያሻው እንደ ምትሃት በጠላት ፊት እየተንጎማለለ ሀገሩን ነፃ ያወጣ ጎረምሳ፡፡ ጃገማ ኬሉ ! የበጋው መብረቅ ! ድንገት ዱብ ባዩ ! ያው የዘር ፖለቲካ ሀገራችን ውስጥ እንደ አስፈሪ ጡር ተመዞ የሚወጋው እየፈለገ ነው፡፡ – ግማሹ “ኢትዮጵያ የፅድቅ ሀገር ነበረች አሁንም ናት” ሲል – ሌላው “የለም! የለም! የብሄር ብሄረሰቦች አስር ቤት ነበረች አሁን ግን የብሄር ብሄረሰብ ሙዚየምነቷን አረጋግጣለች ይላል፡፡” – ግማሹ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ሲል ቀሪው ደግሞ “ወዴት! ወዴት! ጎሳየ ለኔ ህይወቴ” ብሎ ጎሳውን በሃሳብ ይደጉማል፡፡ – “የኢትዮጵያ ታሪክ በመደብ ጭቆና የተሞላ ነው” ሲል ‘ማርክሲስት’ ነኝ ባዩ – “አይ ! የቅኝ ግዛት ነበር” ይላል ተገንጣዩ – አስንጣዩ (የደረግን ሀረግ ለመዋስ)፡፡ የሆነ ሁኖ ነጭ እና ጥቁር የታሪክ ትርጓሜ ይሄው እንደ ውርስ ሀጢያት አልወርድ ብሎ እሳቱም እየጋመ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ምን ይሆን? ሲባል መልሱን እንደ ጃገማ ኬሎ አይነት አኩሪ ጀግኖች ናቸው ሊመልሱት የሚችሉት፡፡ ጀነራል ጃገማ “ነጭ ጤፍ ከጥቁር እንደማይለይ ኢትዮጵያዊያንን ማለያየት አይቻልም!” በሚል ርዕስ በ1986 “ኢትዮጵያዊነት” የተባለ ድርጅት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ያደረጉት ንግግር፡፡ እነሆ ፡ የኢትዮጵዊነት አላማ በኔ አሰተያየት፡- የኢትዮጵያ አንድነት እና ነፃነት እኩልነት ከተጠበቀ በተፈጥሮ ሃብት የተደላደለች በታሪኳ የነነች ኢትዮጵያ ሳትከፋፈል እና ሳትቆራረስ ለዘላለም እንድትኖር የጎሳ ልዩነት ሳይ...
ሃ ገ ሬ By Gebrekirstos Desta
- Get link
- X
- Other Apps
አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት። አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ። አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ። ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም። አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት። እዚያ አለ ነጻነት። በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣ እዚያ አለ ነጻነት። አገሬ ሃብት ነው። ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ። ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ። እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣ ሙዚቃው ያረካል፣ ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል። እዚያ ዘመድ አለ። ሁሉም የናት ልጅ ነው፣ ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣ ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ። ገነት ነው አገሬ። ምነው ምን ሲደረግ ! ምነው ! ለምን ! እንዴት ! ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት። እምቢኝ አሻፈረኝ ! አሻፈረኝ እምቢ ! መቅደስ ነው አገሬ፣ አድባር ነው አገሬ። እናትና አባት ድኸው ያደጉበት ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት አፈር የፈጩበት፣ ጥርስ የነቀሉበት። አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ በቀይ የተጌጠ ባ...
ሁለት ፕሮፌሰሮች፡– ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ By Prof. Mesfin W/mariam
- Get link
- X
- Other Apps
በአንድ ሰኮንድ ውስጥ ስንት ነገሮች ስንት ሁኔታዎች ይታያሉ?፣ ስንት ድርጊቶች፣ ስንት ሥራዎች ይፈጸማሉ? ስንት ሰዎች ይሞታሉ? ስንት ሰዎች ይወለዳሉ? … አንድ ሰኮንድ ባዘለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የስድሳ ሰኮንዶችን ያህል ጥያቄዎች ይፈለፈላሉ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ 60*60= 3600 እነዚህ ደግሞ በ24 ሰዓት ሲባዙ 86 400 ይሆናሉ፤ የሚሆኑትንና የሚደረጉትን ነገሮች ሁሉ መዝግቦ፣ የሚነገሩትን ነገሮች ሁሉ አጣርቶ ይዞ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ አለ ወይ? የትናንትናውን ሃያ አራት ሰዓት በዘርዝር ማስታወስ የሚችል አለ ወይ? ጊዜውና መሣሪያው ያላችሁ የሳምንቱን፣ የወሩን፣ የዓመቱን ሰኮንዶችና ያቀፉትንና ያዘሉትን ጉዳዮች አጣርታችሁ ለማወቅና ‹‹ተረቱንና ታሪኩን›› ለመለየት ሞክሩ፡ እንደኔ የጂኦሎጂ ሀሁ የሚያውቅ ደግሞ ሌላም ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል፤ በጂኦሎጂ ታሪክ የሚቆጠረው በሚልዮን ዓመታት ነው፤ የዛሬ መቶ ሚልዮን ዓመት ምድር እንደዚህ ነበረች፤ ከዚያ በኋላ በዚህ፣ በዚህ ተለዋወጠች እያለ ይነግረናል፤ ተረት ነው የምንለው ወይስ ታሪክ? እንዲያውም አንድ እውነት ልንገራችሁ፤ አሜሪካ አኔ በተማርሁበት ዩኒቨርሲቲ አንድ በበረዶ ድንጋይ በዓለም የታወቀ ፕሮፌሰር ነበረን፤ አንድ ቀን ለመስክ ጥናት ወስዶን አንድ አነስ ያለ ሐይቅ ያለበትን ረባዳ መሬት ቁለቁል እያሳየን የድንጋይ በረዶው ከየት ተነሥቶ ወዴት ሲንሸራተት እንደነበረና ምን እንዳገደውና ሐይቁ እንዴት እንደተፈጠረ ነግሮን ሲጨርስ አጠገባችን ቆሞ ሲያዳምጥ የነበረ የአካባቢው ሰው ድምጹን ከፍ አድርጎ ‹ይህንን ሐይቅ የሠራነው እኛ ነንእኮ!› አለ፤ የኛ ዓለም ያደነቀው ፕሮፌሰር ሁለቱንም እጆቹን ወደሰማይ ዘርግቶ፣ ያውላችሁ የኔ ሀሳብ ብትንትኑ ወጣ...
ዜግነትና የስደተኞች መብትና ግዴታ By Prof. Mesfin W/mariam
- Get link
- X
- Other Apps
መስፍን ወልደ ማርያም የካቲት 2009 ስደተኞች ወደኢትዮጵያ የሚልኩት ጠገራ ብር ብዙ እንደሆነ አውቃለሁ፤ አንዳንድ ስደተኞች ለእንደኔ ያለ ወገኖቻቸው በብዙ መንገድ እርዳታ እንደሚያበረክቱ አውቃለሁ፤ በአንጻሩም አንዳንድ ስደተኞች ትንሽ ጠገራ ብር ይዘው መጥተው የሀኪም ቤትና ሌላም ዓይነት የንግድ ድርጅት (ሀኪም ቤቱን ከንግድ ጋር ያገናኘሁት አውቄ ነው) እያቋቋሙ ደሀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየገፈፉ የሚከብሩም እንዳሉ አውቃለሁ፤ ስደተኞች በአጠቃላይ ለአገራቸውና ለወገናቸው መብት በፖሊቲካው መስክ የሚያደርጉትን ትልቅ አስተዋጽኦ አውቃለሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የሚከነክነኝ ነገር አለ፡፡ ለእኔ ዜግነት ማለት የአገር ባለቤትነት ነው፤ የአገር ባለቤትነት መብቶችንና ግዴታዎችን ያጎናጽፋል፤ አንድ ሰው ስደተኛ ሲሆን የተወለደበትን አገር ባለቤትነት ከነመብቶቹና ግዴታዎቹ በፈቃዱ ትቶ ለሌላ አገር የሚያስረክብ ይመስለኛል፤ እዚህ ላይ የሕግ ጨለማ ውስጥ እንደገባሁ ይሰማኛል፤ አንደኛ ስደተኞች ሁሉ በድሎት አልወጡም፤ ሁለተኛ ስደተኞች ሁሉ ዜግነታቸውን በወጉ አልለወጡም፤ ብዙ ስደተኞች ለአገራቸውና ለወገናቸው ያላቸው የፍቅር ስሜት ገና አልደበዘዘም፤ ይህ ሁሉ እውነት ቢሆንም አንዳንድ ስደተኞች ሀብት የማግኘት ትንሽ ፍንጭ ሲያዩ ከአገራቸው የተሰደዱበት ፍርሃትና ስጋት፣ ለአገዛዙ ካላቸው ጥላቻ ጋር ሙልጭ ብሎ ከውስጣቸው ይወጣና ያላቸውን ቀርቅበው ወደአገር ቤት ይመጣሉ፤ በአገዛዙ በኩል ስለሚፈጥሩት ቁርኝት ምንም መናገር አልፈልግም፡፡ ሌላ በአንዳንድ ስደተኞች ላይ የሚታይ ከስግብግብነት የባሰ ራስ-ወዳድነትና ብልጣብልጥነት አለ፤ ቤት ወይም ትንሽ መሬት በስማቸው ያለ ወላጆች ሲሞቱ ለቀብር ያልተገኙት ስደተኞች ንብረት ለመካፈል ከተፍ ይላሉ! አገር ቤት ሆነው ደፋ ቀና እያሉ ወላጆቻቸውን ያስ...
የሕይወት ዋጋ By Prof. Mesfin W/mariam
- Get link
- X
- Other Apps
በ2009 ዓ.ም. ቆሼ የሚባል ሰፈር ወይም መንደር ተፈጠረ፤ ቆሼ ማለት ቆሻሻን ማቆላመጫ ነው፤ ቆሻሽዬ ማለት ነው፤ ቆሼ የቆሻሻ ተራራ ነው፤ በዚያ የቆሻሻ ተራራ ዙሪያ መሄጃ የሌላቸው ሰፈሩበት፤ ጥንት ሴትዮዋ እንዳለችው፡- እሾህ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው! ሴትዮዋ ይህንን ያንጎራጎረችው ከብዙ ትውልዶች በፊት ነው፤ ጉልበተኞች የኢትዮጵያን ሰዓት ሰንገው ስለያዙት አይነቀነቅም! ባለህበት ሂድ! ነው፤ ዛሬም መሄጃ የለም፤ ቆሻሻንም የሙጢኝ ቢሉ ማምለጥ አይቻልም፡፡ እነዚህ አንድ መቶ አሥራ ሦስት ሟቾች በርግጥ ሰዎች ናቸው? በርግጥ ኢትዮጵያን ናቸው? የምናገረው ጠፍቶኛልና ጥያቄዎች ብቻ ልጠይቅ፡– ቤታቸውን ጉልበተኞች አፍርሰውባቸው፣ መሬታቸውን ሰማይ-ጠቀስ ወይም መንገድ ለመሥራት መሬታቸውን ወስደውባቸው የሚደርሱበት አጥተው፣ ባዶ ቦታ ፈልገው የፕላስቲክ መጠለያቸውን እየሠሩ ግፍን አሜን ብለው በሰላም ተቀብለው ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል እያሉ ቀኖችን ሲቆጥሩ ቆሻሻ መጣያው ደባል የሆነባቸው መቼ ነው? ወይስ ቆሻሻ መጣያው ቀድሞ እነሱ ደባል ሆነውት ነው? ጥያቄው ማን ቀደመ ሳይሆን ቆሻሻውና መጠለያ ፈላጊዎቹ አብረው አንዲኖሩ ፈቃድ የሰጣቸው ማን ነው የሚል ነው? የመጠለያ ፈላጊዎቹን ቤት ያፈረሰውና የቆሻሻውን ተራራ የሚክበው ጉልበተኛ ወይም ጉልበተኞች የተለያዩ ናቸው? ወይስ አንድ ነው? አንድ ከሆነ እውር-ደንቆሮ ሳይሆን አይቀርም፤ በማን-አለብኝነት ልባቸው ያበጠ ግዴለሾች ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ አንድ መቶ አሥራ ሦስቱና ሌሎቹም ዜጎች ቢሆኑ፣ ማለት የአገሩን ባለቤትነት ከጉልበተኞች ጋር በእኩልነት የሚጋሩ ቢሆኑ፣ ሌሎች ዜጎች እነዚህ በቆሻሻ የተበሉት ወገኖቻቸው መሆናቸውን ቢገነዘቡ ቆሻሻና ዜግነት እንደተደባለቁ ማወቃቸው ይቀራል? ዋናው ...
የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት መስፍን ወልደ ማርያም
- Get link
- X
- Other Apps
የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን በአሸነፈች ጊዜ ደግሞ በቴክሳስ የሚኖር ከአንድ ግሪክ ገንፍሎ የወጣው ንግግር በጣም ልብን የሚነካ ነበር፤ ለዚህ አርመንና ለዚህ ግሪክ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዘር የተላለፈላቸው አይመስለኝም፤ ስለዚህም አሜሪካ የሚወለዱትም ኢትዮጵያውያን ልጆች እናቶቻቸው ሳያውቁ ከውስጣቸው የሚያስተላልፉላቸው ስሜት ኢትዮጵያዊነታቸውን ይገነባው ይሆናል፤ እንደሚመስለኝ የሚሞቱለት መሬት ከውስጥ ከነፍስ ጋር በተገናኘ ስሜት የተቆራኘ ነው፤ መሬቱንና ስሜቱን ምን አገናኛቸው? ምን አቆራኛቸው? እንዴት ተቆራኙ? የሚሉትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር እዚህ ቦታው አይደለም፤ ለዚች መሬት የሞቱላት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸውን አምነን በመቀበል እንነሣ፤ ምናልባትም አብዛኛዎቹ ቁራጭ መሬትም አልነበራቸውም፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ለመቃብር ያህል ሁለት ክንድ መሬት አንኳን አላገኙም፤ በተሰለፉበት ወድቀው...