Posts

20/80 ኮንደሚኒዬም የአሸናፊዎች ዝርዝር የካቲት 2011 20/80 Condominium Winners List 2019 March

Image

20/80 Condominium Winners List 2019 March 20/80 ኮንደሚኒዬም የአሸናፊዎች ዝርዝር 2011 የካቲት

Image

20/80 Condominium Winners List 2019 March 20/80 ኮንደሚኒዬም የአሸናፊዎች ዝርዝር 2011 የካቲት

Image

A Memoir of First US Diplomat’s Meetings With Emperor Menelik

Image

ሐተታ አድዋ በ በእውቀቱ ስዩም

የአድዋ ድልን ከድንበር ሉአላዊነት ጋር አያይዞ መተንተን የተለመደ ነው፡፡ ድሉ አነሠ በዛ የሚለው ጭቅጭቅ ከዚህ መሠረት ይፈልቃል፡፡ በኔ ግምት የአድዋ ድል ትልቅ ጭብጥ ‹‹የሰውነት ክብር›› ይሰኛል፡፡ ቀደምቶቻችን ወደ አድዋ የጋለቡት በግፍ የተነጠቁትን የሰውነት መታወቂያ ለማስመለስ ነው፡፡ እንዲያውም ሰው መሆናቸውን በማያዳግም መንገድ ያረጋገጡት አድዋ ላይ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ወገኖቼ!! ሰው መሆንን ማረጋገጥ ቀላል ነገር አይምሰላችሁ፡፡ አባቶቻችን ከአውሮፓውያን ጋር የሚጋሩትን ግን ደግሞ ከአውሮፓውያን ቀድመው የሚያውቁትን ቅዱስ መጽሐፍ ጠቅሰው ሁላችንም ያዳም ልጆች ነነ ይሉ ነበር፡፡ እና ያዳም ልጆች ነነ ብለው የሚያምኑ ፈረንጆች ቢቸገሩ የሚደርሱላቸው፣ ቢጠቁ የሚታደጓቸው ወንድሞቻቸው እንደሆኑ ያስቡ ነበር፡፡ በርግጥም የሃይማኖት አንድነት የቀለም ልዩነትን ደምስሶ አዳማዊ ወንድማማችነትን ያስገኘበት የዘመን ምዕራፍ ነበር፡፡ ክርስቶፈር ደጋማ የተባለ የፖርቹጋል ነፍጠኛ ለኢትዮጵያ ደሙን ያፈሰሰው የማተብ አንድነት ስለገፋፋው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ባንድ ወቅት የሚያገለግል የኑሮ ዋስትና በሌላው ዘመን አያገለግልም፡፡ ሁላችንም ያዳም ልጆ ነነ የሚለው የዝምድና ውል ከእለታት አንድ ቀን ያገልግሎት ዘመኑ አለቀ፡፡ በ1548 ተወልዶ በ1600 እንደጧፍ የተቃጠለው ዦርዳኖ ቡርኖ የተባለ የጣልያን መናፍቅ ‹‹ኢትዮጵያውያን ያዳም ልጆች አይደሉም፤ ቅድመ-አዳማዊያን ናቸው እንጂ›› ብሎ ፃፈ፡፡ በቡርኖ ዘመን ኢትዮጵያ የጥቁር ዘር ሁሉ የወል ስሙ ነው፡፡ ቅድመ አዳማዊ ማለት ደሞ በአዳምነት ማዕረግ ያልደረሠ ጅምር ፍጡር ማለት ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ ጥቁሮች በእግዜር አምሳል የተፈጠሩ አይደሉም የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሳል፡፡ ያለማለዘቢያ ለመግለፅ፣ ጥቁሮች ከእንሥሣትና...

መግለጫ በኢትዮጵያ፡ ትናንት እና ዛሬ By Zelalem Kibret

የጋዜጣዊ መግለጫ እና የአቋም መግለጫ ነገር ሁሌ እንዳስገረመኝ ነው፡፡ እንዴት  ብሎ መጠየቅ  መልካም ነው አበው እንደሚሉት “መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ” ነውና ነገሩ፡፡ ደስታ ተክለወልድ   “ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት” በተሰኝው መፅሃፋቸው   መግለጫ የሚለውን ቃል “ማስታወቂያ  መንገሪያ  ነገር ወይም  የመጽሐፍ  መግለጫ ለጠንቋይ የሚሰጥ ገንዘብ ነው” ብለው ይፈቱታል፡፡ ይህ ትርጉም በዕውነት መግለጫ አሁን ካለው ትርጉም በ እጅጉ ይርቃል ዛሬ መግለጫ ሌላ ናት እንደ ሃሳብን ማስታወቂያ እንደ ሆኔታን መገምገሚያ ፡፡ “መግለጫዎችን” ስሰማ ግራሞቴን የሚጭሩት የቃላቶቹ አመራረጥ፣ የሃሳቦቹ አስቂኝነት፣ የባለ መግለጫዎቹ ማንነት ወዘተ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ደርግ እንዲህ ብሎ መግለጫ ይሰጥ ነበር” <<በጩኸት የፈረሰች ከተማ እያሪኮ ብቻ ነች !!!>> <<ነጭ ኑግ ጥቁር ወተት አቅርቡልኝ ለሚል ህዝብ አቢዮታዊ እርምጃ እንጅ በ Demand-Supply ጨዋታ ጊዜያችንን አናጠፋም !!!>> <<የመርጦ ለማሪያም ከተማ ህዝብ የሬጋንን አስተዳደር አወገዘ የአለም ሰራተኞችም እንዲተባበሩ ጋበዘ!!! >> … እነ ጋሽ መለስ ወደ ስልጣን መጡና ደግሞ ህዝቡን “ልማት ወይም ሞት” ምናምን ብለው አስጨፈሩት መግለጫቸውንም እንዲህ አስከተሉ: ዘንድሮ በተከበረው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ላይ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ ♥ እኛ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች  ምንም እንኳን  ♥ፍቅራችን♥ የ 20 ዓመት (ከ1983 ዓ.ም) ለጋ ፍቅር ቢሆንም፣ ♥በፍቅራችን♥ መሃል የሚገቡት...

የበጋው መብረቅ ይናገራል By Zelalem Kibret

በ15 ዓመት ዕድሜው ጠላትን እፋለማለሁ ብሎ የተነሳ፣ ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ ጠላት ሊይዝ ሲያሳድደው ሲያሻው ጭልሞ ጫካ ውስጥ ዛፍ ላይ መሰላል ሰርቶ እየተደበቀ፣ ሲያሻው እንደ ምትሃት በጠላት ፊት እየተንጎማለለ ሀገሩን ነፃ ያወጣ ጎረምሳ፡፡ ጃገማ ኬሉ ! የበጋው መብረቅ ! ድንገት ዱብ ባዩ ! ያው የዘር ፖለቲካ  ሀገራችን ውስጥ እንደ አስፈሪ ጡር ተመዞ የሚወጋው እየፈለገ ነው፡፡ – ግማሹ “ኢትዮጵያ የፅድቅ ሀገር ነበረች አሁንም ናት” ሲል – ሌላው “የለም! የለም! የብሄር ብሄረሰቦች አስር ቤት ነበረች አሁን ግን የብሄር ብሄረሰብ ሙዚየምነቷን አረጋግጣለች ይላል፡፡” – ግማሹ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ሲል ቀሪው ደግሞ “ወዴት! ወዴት! ጎሳየ ለኔ ህይወቴ” ብሎ ጎሳውን በሃሳብ ይደጉማል፡፡ – “የኢትዮጵያ ታሪክ በመደብ ጭቆና የተሞላ ነው” ሲል ‘ማርክሲስት’ ነኝ ባዩ – “አይ ! የቅኝ ግዛት ነበር” ይላል ተገንጣዩ – አስንጣዩ (የደረግን ሀረግ ለመዋስ)፡፡ የሆነ ሁኖ ነጭ እና ጥቁር የታሪክ ትርጓሜ ይሄው እንደ ውርስ ሀጢያት አልወርድ ብሎ እሳቱም እየጋመ  ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ምን ይሆን? ሲባል መልሱን እንደ ጃገማ ኬሎ አይነት አኩሪ  ጀግኖች ናቸው ሊመልሱት የሚችሉት፡፡ ጀነራል ጃገማ   “ነጭ ጤፍ ከጥቁር እንደማይለይ ኢትዮጵያዊያንን ማለያየት አይቻልም!” በሚል ርዕስ በ1986 “ኢትዮጵያዊነት” የተባለ ድርጅት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ያደረጉት ንግግር፡፡ እነሆ ፡ የኢትዮጵዊነት አላማ በኔ አሰተያየት፡- የኢትዮጵያ አንድነት እና ነፃነት እኩልነት ከተጠበቀ በተፈጥሮ ሃብት የተደላደለች በታሪኳ የነነች ኢትዮጵያ ሳትከፋፈል እና ሳትቆራረስ ለዘላለም እንድትኖር የጎሳ ልዩነት ሳይ...

ሃ ገ ሬ By Gebrekirstos Desta

አገሬ ውበት ነው  ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት  ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።  አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ። አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ  አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ። ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም  ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም። አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት  በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።  እዚያ አለ ነጻነት። በሃገር መመካት፣  በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣ እዚያ አለ ነጻነት።  አገሬ ሃብት ነው። ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ። ጠጁ ነው ወለላ  ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ።  እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣ ሙዚቃው ያረካል፣  ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።  እዚያ ዘመድ አለ። ሁሉም የናት ልጅ ነው፣ ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣ ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር ባለጋራም ቸር ነው  “ያገር ልጅ ሲቸገር” ። ገነት ነው አገሬ።  ምነው ምን ሲደረግ ! ምነው ! ለምን ! እንዴት !  ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ  ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ  የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።  እምቢኝ አሻፈረኝ ! አሻፈረኝ እምቢ ! መቅደስ ነው አገሬ፣ አድባር ነው አገሬ።  እናትና አባት ድኸው ያደጉበት  ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት አፈር የፈጩበት፣  ጥርስ የነቀሉበት። አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ በቀይ የተጌጠ ባ...

Imperial Ethiopia

Image

Semina Work By Loret Tsegaye G/medhin

Image

To All By Loret Tsegaye G/Medhin

Image