Popular posts from this blog
የበጋው መብረቅ ይናገራል By Zelalem Kibret
በ15 ዓመት ዕድሜው ጠላትን እፋለማለሁ ብሎ የተነሳ፣ ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ ጠላት ሊይዝ ሲያሳድደው ሲያሻው ጭልሞ ጫካ ውስጥ ዛፍ ላይ መሰላል ሰርቶ እየተደበቀ፣ ሲያሻው እንደ ምትሃት በጠላት ፊት እየተንጎማለለ ሀገሩን ነፃ ያወጣ ጎረምሳ፡፡ ጃገማ ኬሉ ! የበጋው መብረቅ ! ድንገት ዱብ ባዩ ! ያው የዘር ፖለቲካ ሀገራችን ውስጥ እንደ አስፈሪ ጡር ተመዞ የሚወጋው እየፈለገ ነው፡፡ – ግማሹ “ኢትዮጵያ የፅድቅ ሀገር ነበረች አሁንም ናት” ሲል – ሌላው “የለም! የለም! የብሄር ብሄረሰቦች አስር ቤት ነበረች አሁን ግን የብሄር ብሄረሰብ ሙዚየምነቷን አረጋግጣለች ይላል፡፡” – ግማሹ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ሲል ቀሪው ደግሞ “ወዴት! ወዴት! ጎሳየ ለኔ ህይወቴ” ብሎ ጎሳውን በሃሳብ ይደጉማል፡፡ – “የኢትዮጵያ ታሪክ በመደብ ጭቆና የተሞላ ነው” ሲል ‘ማርክሲስት’ ነኝ ባዩ – “አይ ! የቅኝ ግዛት ነበር” ይላል ተገንጣዩ – አስንጣዩ (የደረግን ሀረግ ለመዋስ)፡፡ የሆነ ሁኖ ነጭ እና ጥቁር የታሪክ ትርጓሜ ይሄው እንደ ውርስ ሀጢያት አልወርድ ብሎ እሳቱም እየጋመ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ምን ይሆን? ሲባል መልሱን እንደ ጃገማ ኬሎ አይነት አኩሪ ጀግኖች ናቸው ሊመልሱት የሚችሉት፡፡ ጀነራል ጃገማ “ነጭ ጤፍ ከጥቁር እንደማይለይ ኢትዮጵያዊያንን ማለያየት አይቻልም!” በሚል ርዕስ በ1986 “ኢትዮጵያዊነት” የተባለ ድርጅት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ያደረጉት ንግግር፡፡ እነሆ ፡ የኢትዮጵዊነት አላማ በኔ አሰተያየት፡- የኢትዮጵያ አንድነት እና ነፃነት እኩልነት ከተጠበቀ በተፈጥሮ ሃብት የተደላደለች በታሪኳ የነነች ኢትዮጵያ ሳትከፋፈል እና ሳትቆራረስ ለዘላለም እንድትኖር የጎሳ ልዩነት ሳይ...
የአቶ አስገደ ልጆች ምን ወንጀል ሠሩ? (አሕለፎምና የማነ አስገደ) መስፍን ወልደ ማርያም
አቶ አስገደ ከቀደሙት የወያኔ ታጋዮች አንዱ ነው፤ ወያኔ ለሥልጣን እስከበቃበትና ከዚያም አልፎ አባል ሆኖ ቆይቶአል፤ በኋላ ግን የተመለከተውን አሠራርና አካሄድ እየተመለከተ ወያኔ ዱሮ የነበረውን ዓላማ በሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ከሚደረገው ጋር ሲያነጻጽር መነሻውን እየሳተ መሆኑን በመገንዘቡ የወያኔን አሠራር በቁጭት መተቸትና መንቀፍ ጀመረ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፎችንም ደረሰ፤ አጫጭር ጽሑፎችም በጋዜጦችና በመጽሔቶች ላይ ጻፈ፤ ከጓደኞቹ ከቀድሞ የወያኔ አባሎች ጋር በመሆን አሬና የሚባል ተቀናቃኝ ፖሊቲካ ፓርቲ አባል ሆነ፤ ይህ ሁሉ እንደሰውም፣ እንደዜጋም የአቶ አስገደ መብቱ ነው፤ ወያኔን በመተችትና በመንቀፍ አቶ አስገደ የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻውም እንደማይሆን እየታየ ነው፤ ከዚህ በፊት አቶ ገብረ መድኅን አርአያ ወያኔን ሲያጋልጥ ቆይቷል፤ አሁንም እየቀጠለ ነው፤ አሁን ደግሞ ከአቶ አስገደ ጋር ኤንጂኒር አብደልወሃብ ቡሽራ አለ፤ … እውነት የብረት ግንብም ቢሆን ሰርስሮ የመውጣት ኃይል አለው፤ እየወጣም ነው፡፡ በሚያዝያ (2005) ውስጥ የአቶ አስገደ ሁለት ወንዶች ልጆቹ ከተለያዩ ከተሞች ተይዘው ታሰሩ፤ አቶ አስገደ እንዳለው አንዱ ልጁ፣ አሕለፎም አስገደ ሚያዝያ 16/2005 ‹‹በአንድ ሻይ ቤት ቡና ሲጠጣ›› ተያዘ፤ ሌላው ልጁ ደግሞ፣ የማነ አስገደ የሚባለው የሶፍትዌር ኤንጂኒር ታሞ ስለነበረ ጠበል ለመጠመቅ ወደአያቱ መኖሪያ ሄዶ ሳለ በሚያዝያ መጨረሻ ሳምንት አካባቢ ተይዞ ታሰረ፤ የሁለቱ የአቶ አስገደ ልጆች በሚያዝያ 16ና ምናልባትም 25 መሀከል በሁለት በተለያዩ ከተሞች ተይዘው መታሰር አድፍጦ የሚጠብቃቸው ኃይል የነበረ ያስመስለዋል፤ ልጆቹ ከወያኔ ድርጅት ጋር ያላቸው/የነበራቸው ግንኙነት አይታወቅም፤ አባታቸው አቶ አስገ...
Comments
Post a Comment